መታወቂያ
  ገጽየቫቲካን
  ሬድዮ ጣቢያ
የቫቲካን
  ሬድዮ ጣቢያ

ክፍሎች


  የፍቅር ሥራና ትብብር


  ቤተ ክርስቲያን


  ባህልና ኅብረተ ሰብ


  የቫቲካን ሰነዶች


  ሲኖዶስ


  የኣብያተ ክርስትያናት
   ኣንድነት



  ቤተ ሰብ


  ወጣቶች


  ፍትህና ሰላም


  ፖለቲካ


  ሃይማኖትና ውይይት


  ሥነ እውቀትና
   ግብረ-ገብነት



  ጕባኤ ኣስተምህሮና ጸሎተ
   መልአክ እግዚኣብሔር



  ሐዋርያውያን ጕብኝቶች


cx_t06


መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን > ዜና


02/11/2009 12.40.25



የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት







ሙሊየሪስ ዲግኒታተም፣ የሴቶች ክብር በሚል ርእስ ሥር ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግምዊ የደረስዋት ሓዋርያዊ መልእክት 20ኛው ዓመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ ከ የካቲት 7 ቀን እስከ የካቲት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ያወታውን የማጠቃላያ ሰንድ ያካተተ፣ ሴት እና ወንድ፣ የሰብአዊነት ሙላት በሚል ርእስ ሥር አንድ መጽሓፍ ለሕትመት ማብቃቱ ዜኒት የዜና አገልግሎት ካሰራጨው ዜና ለማወቅ ተችለዋል።

ይህ በቫቲካን ማተሚያ ቤት የታተመው መጽሓፍ የመጀመሪያ ሕትመቱ በጣሊያንኛ ቋንቋ ሲሆን፣ በቅርቡ በስፓኒሽ በእንግሊዝኛ እና በፈረንሳይኛ ተተርጉሞ ለሕተመት እንደሚበቃ ዜኒት አስታወቀ። ስነ ሰብአዊ ጥናት መሠረት የሚገለጠው የሴት የሴትነት ባህርይ የሚያጎላ ከኅብረተሰብ እና ከባህል የሚሰጣት የተጽእኖ ባህርይ አንድ በአንድ በመለየት የሴት እውነተኛው ሴት በመሆንዋ ላይ ያለው የሴትነት ባህርያዋን የሚተነትን እና ሴተ እና ወንድ የስብአዊነት ሙላት መሆናቸው በሚገልጥ ሀሳብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቫቲካን እ.ኤ.አ. ከየካቲት 7 ቀን እስከ የካቲት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ተካሂዶ ለነበረው ዓውደ ጥናት፣ የክርስትያናውን ባህል አዲሱ ዘመን እና የስነ ምርምራ እድገት በማነጻጸር ባስተላለፉት መልእክት ያስተላለፉት ትምህርት ያካተተ ነው።

በተለያዩ ስለ ሰብአዊ ክብር ስለ ሴት እና ወንድ መብት እና ፈቃድ እንዲሁም ክብር ርእስ በማድረግ እ.ኤ.አ. በተካሄዱት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ይህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያስላለፈው ያቀረበው መልእክት እና መግለጫ ያካተተ መሆኑም ዜኒት ያረጋገጣል።

የዚህ መጽሓፍ መግቢያ የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ርይልኮ አማካኝነት የተጻፈ ሲሆን፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን ሴት እንዴት ባለ መልኵ እንደምትገለጥ በመተንተን ወንድ እና ሴት በመተባበር ቤተ ክርስትያን ቤተ ሰብ እና ኅበረተሰብን ለመገንባት የተጠሩ መሆናቸው በመተንተን፣ የማንነት መደናገር ለተለያዩ ችግሮች እንደሚያጋልጥ ሰፋ በማድረግ በማስረዳት፣ የሁሉም ሂደት መሠረት ለቅድስና መጠራት ሲሆን፣ ወንድ እና ሴት የሚፈጽሙት ሁሉ ለቅድስና መጠራታቸው ከማመን አኳያ የመነጨ መሆን እንዳለበት የሚገልጥ የመግቢያ መልእክት መሆኑ ዜኒት ያረጋገጣል።


« ወደ ኣርእስት ማውጫው ይመለሱ






02/11/2009 17.02.46
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅድስት መንበር የተመደቡ አዲስ የቡልጋርያ አምባሳደር ተቅብለው አነጋግረዋል


02/11/2009 12.41.26
የክህነት ዓመት፣ ወጣቱ ትውልድ ጥሪውን እንዲለይ መደገፍ



02/11/2009 12.38.56
የሃንጋሪ ቤተ ክርስትያን



28/10/2009 14.09.45
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለሁሉም አርመናውያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ካረኪን ሁለተኛ መልእክት አስተላለፉ



23/10/2009 14.59.43
ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሹመት ሰጡ




እርስ በርስ የታያያዙ ክፍሎች


ያለፈው ገጽ  ያለፈው ገጽ
መታወቂያ
  ገጽ  መታወቂያ ገጽ
ለዝግጅት
  ክፍል ይጻፉ  ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ
top
top
All the contents on this site are copyrighted . Webmaster / Credits / Legal Conditions
top
top